Search
Close this search box.

ግሎባል ባንክ የሚሰራው የ ‹‹ ቂርቆስ ፓርክ ›› ስራ በይፋ ተጀመረ !!

Share the Post:

በትላንትናው ዕለት የደቡብ ግሎባል ባንክ ቺፍ ፋይናንስና ሰፖርት ሰርቪስ ኦፊሰር አቶ ዳሳ ጎቤ እና ሌሎች የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የወረዳ 4 ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ናሆም መንግስቱን ጨምሮ በቂርቆስ ክ/ከተማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፋና ታደሰ በተገኙበት ፓርኩን ለማልማት ውድድሩን ላሸነፈውና በፓርክ ልማት ሰፊ ልምድ ላለው ‹‹ ሮዝሜሪ ግሪን ላንድ ›› ለተባለ ተቋም በማስረከብ ስራውን በይፋ አስጀምረዋል ፡፡
አቶ ዳሳ እንደገለፁት ይህ ፓርክ የከተማዋን ገፅታ በከፍተኛ ደረጃ የሚቀይር ከመሆኑም በላይ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍና በውስጡ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ባንካችን ልዩ ትኩረት የሚሰጠውና ጥራትና ደረጃውን ጠብቆ መሰራቱን በጥብቅ የሚከታተለው ይሆናል ብለዋል ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሮዝሜሪ ግሪን ላንድ ስራ አስኪያጅ ወ/ት መሰረት ከበደ እንደተናገሩት ከደቡብ ግሎባል ባንክ የተረከብነውን የፓርክ ቦታ በታቀደው ጊዜና በተሰራው ዲዛይን መሰረት ሰርተን ለማስረከብ ዝግጅታችንን ጨርሰን በዛሬው ቀን ስራ ጀምረናል ብለዋል ፡፡

በዕለቱም የአካባቢው ነዋሪዎችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተገኙ ሲሆን ይህን ፓርክ ተጠናቆ ለማየት ከፍተኛ ጉጉት እንዳደረባቸው ገልፀው በውስጡም በሚፈጥርላቸው የስራ እድል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ካደረግንላቸው ቃለ መጠይቅ መረዳት ችለናል ፡፡

ባንካችን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቄራ አትክልት ተራ አካባቢ ለማህበረሰቡ ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጥና የከተማዋን ገፅታ በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀይር ፓርክን ለማልማት ከክፍለ ከተማው አስተዳደር 3,000 ካሬ ቦታ መረከቡ የሚታወስ ነው::

Related Posts