Search
Close this search box.

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ላይ የ 50 ሚሊዬን ብር አክሲዮን ግዥ መፈፀሙን አስመልክቶ የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የፊርማ ሥነ ስርዓት ተከናውኗል፡፡
ካፒታል ገበያ ለባለአክሲዮኖች እንዲሁም ለተለያዩ የባለድርሸ አካላት የሚሰጠውን ጥቅም ጨምሮ ለአገር የኢኮኖሚ ዕድገት የሚጫወተውን ከፍተኛ ሚና በመረዳት ከኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ጋር ለመስራት መወሰኑን የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የኮርፖሬት እስትራቴጂና ትራንስፎርሜሽን አሲስታንት ቺፍ ወ/ሮ መዓዛ ወንድሙ በፊርማ ስነስርዓቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር አመላክተዋል፡፡

ጥላሁን እስማኤል (ዶ.ር) በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ‹‹ የኢትዮጵያ ሴኪዩሪቲ ኤከስቼንጅ ›› ዋና ስራ አስፈጻሚ በበኩላቸው “የአገራችንን የካፒታል ገበያ ለማሳደግና የማህበረሰቡን የንግድ እንቅስቃሴ ወደላቀ ደረጃ ለማድረስና የአገር ኢኮኖሚን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ በምናደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ የባንክ ሴክተሩ ሚና ከፍተኛ ነው” ብለዋል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የገዛው የ50 ሚሊዬን ብር አክሲዮን በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ላይ የአምስት በመቶ ድርሻ እንዲኖረው ያስችለዋል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጰያ
ለጋራ ስኬታችን!